=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
የረመዷ ወር በጣም ርህሩህ ቸር የሆነው አምላካችን አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ወደ እሱ እንድንቀርብ ፣ ከርሱ ጋር ያለንን ትስስር እንድናጠብቅ ፣ ምህረትን እንድንጠይቅ ፣ ለመጭው አለም ስንቅ እንድንይዝ ፣ ስብዕናችነን እንድናስተካክል ፣ አላማችነን እንድንቀርፅ የሰጠን እድል ወይም ስጦታ ነው። ነገርግን አንዳንዶቻችን ይህን የተከበረና የተባረከ ወር ባረባ ነገር አናሳልፈዋልን። አብዛኛዎቹ የምናሳልፍባቸው ነገሮች ደግሞ በረመዷን ወርም ይሁን ከረመዷን ውጭ የአሏህን ሕግ የሚፃረሩና ለአሏህም ትዕዛዝ እንቢተኝነትን የምናሳይባቸው ነገሮች ናቸው። አብዛሀኛዎቹ አለማዊነትን እንጅ መንፈሳዊነትን አያንፀባርቁም። ከነዚህም መካከል የረመዷንን ወር የተለያዩ ፊልሞችን ፣ ተከታታይ ያረብ ድራማዎችን(ሙሰልሰል) ፣ ካርታ ወይም ሌሎች ጌሞችን በመጫወት እና በእንቅልፍ እናሳልፋለን። ከነዚህም በተጨማሪ ቀን ስንጾም ውለን ማታ ስንቅምና ስናጨስ እንገኛለን፤ የሙዚቃ ኮንሰርቶችንና ዉድድሮችን እየከታተልን ጊዜያችነን ባረባ ነገር እናሳልፋለን።
{168} የሰው ልጆች ሆይ! በምድር ውስጥ ህጋዊና ንፁህ የሆነን ነገር ተመገቡ ፤ የሰይጣንንም የእግር ኮቴ አትከተሉ። በእርግጥ እሱ ለናንተ ግልፅ ጠላት ነው።
ይህን አውቀን መጥፎ ነገሮችን ከማየትና ከመስራት ልንቆጠብ ይገባል። እናቶቻችንና እህቶቻችን አብዛሀኛውን ጊዜያቸውን ኩሽና ቤት ውስጥ እናዳያሳልፉ የተወሰኑ ስራዎችን ልናግዛቸው ይገባል።
የረመዷን ወር ስብዕናችነን የምናስተካክልበት ፣ አላማችነን የምንቀርፅጽበት ፣ እስላማዊ ወንድማማችነትንና እህትአማችነትን የምናሳይበት ፣ የረሱልን ሱና አጥብቀን የምንይዝበት ፣ ከአሏህ ጋር ያለንን ግኑኝነትና ትስስር የምናጠናክርበት እና ለመጭው አለም ስንቅ የምናዘጋጅበት ወር ከሆነ ይህን ወር እንዴት ማሳለፍ እንዳለብን ራሳችነን ከወዲሁ ልንጠይቅ ይገባል። በዚህ በተከበረ ወር ውስጥ ላሉ የጊዜ ክፍልፋዮች ማለትም ለእያንዳንዷ ሰከንድ ፣ ደቂቃ ፣ ሰዓት ፣ ቀን ፣ ሳምንት እና ሳምንታት ውስጥ ለምንሰራቸው ስራወች ወጋ ልንሰጥ <<ቀንህ እድሜህ ነው>> የሚለውን አባባል ስንቅ አድርገን ልንይዝ ይገባል።
በረመዷን ወር የምንሰራቸውን ስራዎች ዘርዝረን ለእያንዳቸው ሰዓት በመመደብና በመደብንላቸው ሰአት ለማጠናቀቅ መጣጣር ይኖርብናል።
1) መንፈሳዊ ራዕይ
2) የእውቀት ራዕይ
3) የስብእና/የባህሪ ለውጥ ራዕይ
4) ማህበራዊ ራዕይ
ናቸው
መንፈሳዊ ራዕይያችነን ለማሳካት የተለያዩና ዘርፈ ብዙ ስራዎችን መስራት ይኖርብናል። ከነዚህም መካከል:-
√ ቁርአንን በማስተንተን መቅራት
√ ኢስላማዊ እውቀትን መሻት/ኢላስማዊ መፅሐፎችን ማንበብ
√ ሶላትን በኹሹእና በሙሉ አትኩሮት መስገድ
√ ሱና ሶላቶችን ማብዛትና የታራዊህ ሶላትን መስገድ
√ ዚክር ፣ እስቲግፋር እና ኢኽላስ ያለው ዱአን ማብዛት
√ ሐዲሶችን ማንበብ
√ የረሱልን ታሪክ በማንበብ ስብዕናቸውን ለመላበስ መሞከር
√ በነፍሲያችን ላይ በመዝመት የአካል ክፍላችነን መልካም ስራ እዲሰራ ማድረግና ለአሏህ ህግጋት ተገዥ ማድረግ
√ መስጊዶቻችነን መንከባከብ
- ይህም ሲባል ጽዳታቸውን መጠበቅ
- በቻልነው መጠን የጐደላቸውን ነገሮች ማሟላት
√ ህይወትን በቁርአንና በሐዲስ መምራት
√ ከዉሸትና ከሐሜት መራቅ
√ ምላስን ከመጥፎ ነገር መጠበቅ
√ አሏህ ያዘዘንን ነገር መስራት፤ የከለከለንን ነገር መከልከል
√ የረሱልን ሱና መከተል
√ ሰዉ አክባሪ መሆን
√ የተግባር ሰው መሆን
√ ከቢድአ ነገሮች መራቅ
√ ወደ ሃጢያት እንድናመራ የሚደርጉ ነገሮችን በሙሉ መራቅ
√ የአሏህ ፍራቻ በልባችን ውስጥ እንዲኖር ማድረግ
√ ተፈኩር ማድረግ
√ በድብቅ ሶደቃ መስጠት
√ በነፍሳችን ላይ ጅሃድ ማድረግ
√ በለሊት ሶላት መስገድ
√ ከንቱ ንግግርን ማስወገድ
√ ቤተሰቦቻችነን ማገዝ
የስብዕና ወይም የባህሪ ለውጥ ለማምጣት የሚከተሉትን ባህሪያት የራሳችን ለማድረግ መጣር ይኖርብናል።
- ከአሏህ እምነት ያለው መሆን
- ትሁት
- ደግ/ቸር
- ሰው አክባሪ
- ፈገግተኛ
- መልካም ሰሪ
- ሰአት አክባሪ
- ፅኑ
- ትዕግስተኛ
- ከሰው ጋር ተግባቢ
- ተጥራሪ እና ቶበተኛ
- አሏህን ፈሪ
- ታማኝ
- አስተዋይ
- ተጨዋች
- ፍትሀዊ
- ሀቀኛ
- ቅን
- መሃሪ/አዛኝ
- ንቁ
- አዲስ ነገሮችን ለማወቅ ጉጉት ያለው
- ጀግና
- ሂክማ ያለው
- አሏህ በሰጠው ኒእማ የሚብቃቃ
- ታማኝ
- በቃሉ የሚገኝ
- ሃያእ ያለው
- ዝምድናን መቀጠል
- የታመሙትን መጠየቅ
- አንድነታችነን ለማስጠበቅ መስራት
- ፈገግተኝነት እና ለሰወች ቅርብ መሆን
- ጤናማና ዘላቂ የሆነ ማህበራዊ ግኑኝነትን መመስረት
- በየመስጅዶቻችን ያሉ ችግሮችን ለመፍታት መስራት
ከላይ ከጠቀስኴቸው በተጨማሪ እያንዳንዳችን ምንማድረግ እንዳለብን በማሰብና በማስተንተን ጉዞችነን "ሀ" ብለን እንጀምር!!!
By Ahmed Yesuf CEO and Founder of Youth-Mission የወጣቱ ተልእኮ
Like this page:
http://facebook.com/youth.mission29
website:
http://youth-mission.mobie.in
{.♥.° ኑ ስለ ኢስላም እንተዋወስ °.♥.}
'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_
©የወጣቱ ተልእኮ
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|